Print this page
Monday, 28 January 2019 00:00

የሳይበር ሴኪዩሪቲና ዳታ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ስልጠና በአገራችን ሊሰጥ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(2 votes)

በሳይበር ሴኩዩሪቲ፣ ዳታ ሳይንስና በአመራር ጥበቦች ላይ የሚያተኩር ስልጠና በአገራችን ሊሰጥ ነው፡፡ አክት አሜሪካን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በአሜሪካ አገር ከሚገኝና መሃርሺ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሚሰጠውና በአገራችን የመጀመሪያ ቢሆነው በዚህ የሳይበር ሴኩዩሪቲና ዳታ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውና በገበያው ከፍተኛ ተፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚሰሩ የኮሌጁ የሥራ ኃላፊዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡
አክት አሜሪካን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በስራ አመራር፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽንና በኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራትን አላማው አድርጐ መቋቋሙን የተናገሩት የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው አጥናፉ; ኮሌጁ በእነዚህ የትምህርት ዘርፎች ከፍተኛ የድህረ ምረቃ ትምህርቶችን በመስጠት ብቁ ባለሙያዎችን ያስመርቃል ብለዋል፡፡
በአሜሪካ አገር ከሚገኘው መሃርሺ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ይሰራል በተባለው በዚሁ አክት አሜriካን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት በተግባር ላይ ያተኮረና ተማሪዎቹ ብዙ ጊዜያቸውን ተግባራዊ በሆኑ ሥራዎች ላይ እንዲያሳልፉ የሚያደርግ እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ከኮሌጁ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ብቁ ባለሙያዎች የሆኑና ዓይነተኛ ለውጥ የሚያመጡ ይሆናሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
የኮሌጁ የቅበላ መስፈርት ትምህርት ሚኒስቴር የሚይመጣውን የቅበላ መስፈርቶች የሚያሟሉና በኮሌጁ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የቻሉ ሊሆኑ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ኮሌጁ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት እንሚሰራ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ተማሪዎቹ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ካጠናቀቁ በኋላ ለሁለተኛ ዓመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚችሉበት መንገድ እንደሚመቻችም ተናግረዋል፡፡
ኮሌጁ በማስተርስ ደረጃ አስተምሮ ለማስመረቅ እስከ 90ሺ ብር ድረስ ክፍያ እንደሚጠይቅና ይህም ተማሪው የማስተርስ ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ አለምአቀፋዊ እውቅና ያለው ድግሪ ይዞ እስከሚወጣ ድረስ የሚያስፈልገውን ሙሉ ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡  

Read 1176 times Last modified on Saturday, 26 January 2019 15:54