Print this page
Saturday, 02 February 2019 14:43

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ለኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ቀረቡ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት መቅረባቸው ታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ያቀረቡት ዶ/ር ግሩም ዘለቀ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው የእጩነት ጥያቄውን መቀበሉን አረጋግጧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ለሃገራቸው እና ለጎረቤት ሃገራት ሰላም መስፈን ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን፣ በኢትዮጵያ ከስጋት ይልቅ ተስፋ እንዲያብብ ማስቻላቸው በእጩነት ማመልከቻው ተጠቅሷል፡፡
ለሁለት አስርት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር እንዲሁም የአካባቢው ሃገራት መንግስትን ለመሳም እንዲሰሩ አነሳስተዋል የሚለው ለእጩነት ካስቀረባቸው ዋነኛው መሆኑን አመልካቹ ገልፀዋል፡፡ ላለፉት 40 ዓመታት በጥርጣሬ ይተያዩ በነበሩት ሶማሊያና ኢትዮጵያ መካልም መተማመን ፈጥረዋል ተብሏል፡፡
በትጥቅ ጭምር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ኦነግ፣ ኦብነግ አርበኞች ግንቦት 7 እና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሃገራቸው ገብተው፣ በሃገራቸው ፖለቲካዊ ጉዳይ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ እድሉን ማመቻቸታቸው፣ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲሁም ጋዜጠኞችን ከእስር መፍታታቸው ተጠቅሷል፡፡  

Read 8174 times