በምንዳር አለው ዘውዴ በተፃፈውና “አፍን ዘግቶ ፉጨት” በተባለው ልብወለድ መጽሐፍ ላይ በነገው ዕለት ውይይት ይካሄድበታል፡፡
በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት ኤጀንሲ፣ በጀርመን ባህል ማዕከልና በእናት ማስታወቂያ ትብብር የሚዘጋጀው የመፃሕፍት ውይይት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፤ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ለመጽሐፉ የውይይት የመነሻ ሃሳብ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡