Saturday, 09 February 2019 12:20

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት እውቅናና እንዲያገኙ ይሰራል ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)


     “የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር” የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለሃገር አንድነት ለከፈለው መስዋዕትነት ተገቢው እውቅናና ክብር እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት እያደረግኩ ነው አለ፡፡
ማህበሩ ጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተመሰረተ በኋላ ሶስት ያህል ጉባኤዎችን በማካሄድ የአባላት ቁጥሩን ከማበራከት ጎን ለጎን፣ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን የማደራጀትና በኢኮኖሚም የመደገፍ ተግባር ለማከናወን መርሃ ግብር ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የሃገር ባለውለታ የሆኑና በህይወት ያሉም ሆነ የሌሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን የህይወት ታሪክና የሙያ አስተዋፅኦ በጥናትና ምርምር ታግዞ በፅሁፍ፣ በድምፅና በምስል ሰንዶ ታሪካቸውን ለትውልድ ለማስተላለፍ ማህበሩ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
ማህበሩ ሰራዊቱ ለአገር አንድነት የከፈለውን ከፍተኛ መስዋዕትነት በክብር እንዲዘከርና የነበረው መልካም ስምና በጎ ምግባር ጎልቶ እንዲወጣ፣ ተከታታይ ታሪክን የመዘከር ተግባር አከናውናለሁ ብሏል፡፡
ሰራዊቱንና ቤተሰቦቻቸውን ከመደገፍ ባሻገር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ላይም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማህበሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡  

Read 6989 times