Saturday, 09 February 2019 12:52

“አፋን ኦሮሞ አማርኛ- እንግሊዝኛ ለጀማሪዎች ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በሀሮ ቢያንስ የተዘጋጀውና የኦሮምኛ ቃላትን ወደ አማርኛና ወደ እንግሊዝኛ የሚፈታው “አፋን ኦሮሞ አማርኛ እንግሊዝኛ ለጀማሪዎች” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ኦሮምኛን (ቁቤን) በቀላሉ ለመልመድና ወደ አማርኛና እንግሊዝኛ ለመተርጐም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተነገረለት መጽሐፉ ካላቲን የተወረሱ 32 ፊደላትን (ኣርፊሰገሌዋ)ን የሚያስተዋውቅና በተለይ ለአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪ ትልቅ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ በ151 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ71 ብር ይሸጣል፡፡

Read 2198 times