Saturday, 09 February 2019 12:55

“ክስተት” የግጥም መድበል እየተነበበ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በመምህርና ገጣሚ አህመድ መሐመድ (ሸምሰዲን) የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን የያዘው “ክስተት” የግጥም መድበል እየተነበበ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለፍቅር፣ ስለማህበራዊ መስተጋብር ስለሰው ልጅ እኩይና ሰናይ ባህሪና ስለሌሎች በርካታ ጉዳዮቻችን የሚዳሰሱ ከ50 በላይ ግጥሞችን ያካተተው መጽሐፉ በ54 ገፅ ተቀንብቦ በ35 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ገጣሚው ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግና በስነ መንግስት ኮሌጅ በስነ - ዜጋና በስነ - ምግባር ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ በቤተሰብ አካዳሚ በስነ - ዜጋና በስነ ምግባር መምህርነት የሚያገለግል ሲሆን ግጥም ደግሞ የነፍሱ ጥሪ እንደሆነ ገልጿል፡፡

Read 647 times