Sunday, 10 February 2019 00:00

ዳጉ ሚዲያ ፌስቲቫል የየካቲት ወር ፕሮግራም ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ዳጉ ወርሃዊ የሚዲያ ፌስቲቫልና አመታዊ ሽልማት የየካቲት ወር ፕሮግራም ከነገ በስቲያ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኘው አምቢያንስ ሬስቶራንት ይካሄዳል በዳሪክ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም በጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ ዋና አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ዝግጅት ላይ አንጋፋ ጋዜጠኞችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው ልምዳቸውን ያካፍላሉ፣ በወቅቱ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ተስፋዎችና ተግዳሮቶች ላይ ምክክር ያደርጋሉም ተብሏል፡፡
በየወሩ የሚካሄደው የዳጉ ሚዲያ ፌስቲቫል በአመቱ መጨረሻ ለዚህች አገር በመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ድርጅቶችና ግለሰቦች እውቅናና ሽልማት ካበረከተ በኋላ የቀጣዩን አመት ዝግጅት እንደሚጀምር የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ አስታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ደስታ ምትኬም በዕለቱ ይዘክራሉ ተብሏል፡፡

Read 1234 times