Sunday, 10 February 2019 00:00

“የባከኑ ጭኖች”ና “የሞት ጉዞ” መፅሐፎች ሰኞ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲና ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ተፅፎ ለንባብ የበቃው “የባከኑ ጭኖች” የተሰኘው መፅሐፍ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ትንሿ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መፅሐፉ በዋናነት የቤተሰባቸውን ህይወት ለመለወጥ ወደ አረብ አገር ተጉዘው ዕድሜያቸውን እዛው በመፍጀት ሳይማሩ፣ ሳያገቡና ሳይወልዱ ዕድሜያቸውን የጨረሱ ሴቶች ህይወት ላይ እና በራስ ወዳድነት ልጆቻቸውን ወደ አረብ አገር ልከው እነሱ ቁጭ ብለው የሚኖሩ ወላጆች ላይ እንደሚያጠነጥን ደራሲው ገልፀዋል፡፡
በ228 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ120 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ገቢው ሙሉ በሙሉ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ግንባታ ይውላል ተብሏል፡፡ በምርቃቱ እለት ደራሲና ጋዜጠኛው በስደት ያሉ እህቶችን በምክርና በድጋፍ የሚያግዙበት “ፍካት የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር” 4ኛ ዓመት በዓል እንደሚከበር እና በስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ የሚያሳየው የመጀረሙያ መፅሐፋቸው “የሞት ጉዞ”ም እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1382 times