Monday, 11 February 2019 00:00

“መጽሐፈ ፍቅር” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


     ከ1959 እና 60 ዓ.ም ጀምሮ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽኦ በነበራቸው በዚህም እንቅስቃሴ ሲታሰሩ ሲፈቱ ሲሰደዱ በኖሩት እና የ70 አመት የእድሜ ባለፀጋ በሆኑት አቶ ፋንታሁን ጥሩነህ የተፃፈው “መጽሐፈ ፍቅር” የተሰኘው መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ደራሲው በዋናነነት በቀዳማዊ ሃይለስላሴ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) ጀምሮ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ካደረጉት እንቅስቃሴ ከአገር ወጥተው እንስከተሰደዱባቸው ሱዳን፣ ጣሊያን፣ አሜሪካና ካናዳ ያሳለፉትን ልምድና የህይወት ተሞክሮ በስፋት የዳሰሱበት መሆኑን በመግቢያቸው አስፍረዋል፡፡
በ173 ገጽ የተመጠነው መጽሐፉ በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4201 times