Saturday, 16 February 2019 13:52

“በአንዳንድ ፊቶች ፊት” እና “ማተብ እና እንጀራ” የግጥም መድብሎች ተመረቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


       የገጣሚና ጋዜጠኛ ሰለሞን ኃይለየሱስ “በአንዳንድ ፊቶች ፊት” የተሰኘ የግጥም መድበል ባለፈው ሰኞ ምሽት በራስ ሆቴል ተመረቀ፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ፀሐፌ ተውኔት፣ ደራሲና አዘጋጅ አያልነህ ሙላቱ በመፅሐፉ ላይ ስነ ፅሑፋዊ እይታ ያቀረቡ ሲሆን መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ዲስኩር አቅርበዋል፡፡
ገጣሚ ሰለሞን ኃይለየሱስን ጨምሮ ገጣሚና ባለቅኔ ኤፍሬም ስዩም፣ አርቲስት አስቴር በዳኔና ሌሎችም የራሳቸውን ስራዎችና ከመፅሀፉ የተወሰዱ ግጥሞችን ያቀረቡ ሲሆን መድረኩ በአርቲስት ፍቃዱ ከበደ መመራቱና በመሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ መድመቁም ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ የገጣሚ ተስፋሁን ፀጋዬ “ማተብ እና እንጀራ” የተሰኘ የግጥም መፅሐፍ ትላንት ምሽት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የተመረቀ ሲሆን፤ ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ በመፅሀፉ ላይ ሂሳዊ ዳሰሳ አቅርቧል፡፡ በዝግጅቱ ላይ በኃይሉ ገ/እግዚአብሄር ወግ ሲያቀርብ፣ አርቲስት ደረጀ ፍቅሬ፣ ገጣሚ ደምሰው መርሻ፣ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ አርቲስት መኮንን ላዕከና ሌሎች ግጥምና አዝናኝ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡

Read 745 times