Saturday, 16 February 2019 15:05

“ቃልና ቀለም” የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ወርሃዊው “ቃልና ቀለም” ሁለተኛ ዙር የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በዋቢሸበሌ ሆቴል እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡
ባለሙያዎች በምሽቱ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ዲስኩር፣ ገጣሚዎቹ የሻው ተሰማ (የኮተቤው)፣ ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ዘላለም ምህረቱ፣ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ፣ ሙዚቀኛ ዘቢብ ግርማ፣ ገጣሚ ልሳን ሀጎስ ገጣሚ ምስክር ይብራ፣ ገጣሚ ዳግም ህይወትና እዮብ ሙሴ ሥራዎቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን በተስፋሁን ከበደ የአንድ ሰው ተውኔት እንደሚቀርብና ዝግጅቱ በመሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚታጀብ ታውቋል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን መድረኩ በተወዳጅ እሸቱና መቅደላ መኩሪያ እንደሚመራም አዘጋጆቹ ታውቋል፡፡

Read 8269 times