Wednesday, 27 February 2019 12:53

አሸናፊ ግጥሞች

Written by 
Rate this item
(11 votes)


ባወጣው “የመደመር የግጥም ውድድር” በርካቶች  የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ የግጥም ባለሙያዎችና የሥነጽሁፍ ሃያሲያን ግጥሞቹን ገምግመው ከ1ኛ-3ኛ

የወጡትን ይፋአድርገዋል፡፡ አሸናፊዎቹም በቅርቡ በብሔራዊ ቴአትር በተካሄደ “የመደመር” እና የፍቅር የኪነጥበብ ምሽት ላይ ግጥሞቻቸውን ለታዳሚያን እያነበቡ

ሽልማቶቻቸውን ተቀብለዋል፡፡ 1ኛ የወጣው ላፕቶፕ፣ 2ኛ የወጣው ዘመናዊ ስማርት ፎን፣ 3ኛ የወጣው መለስተኛ ስማርት ፎን ተሸልመዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት

3ኛ የወጣውን ያቀረብን ሲሆን ዛሬ ደግሞ 2ኛ የወጣውን እነሆ ብለናል፡፡



ከዋርካው ሥር እንሰብሰብ
ሐገር ፍቅር ደግ’ሣ
ሽርር ጉድ’ስትል በጉጉት የልጆቿን ልብ ልታጠግብ
የሆድ ሳይሆን የሕሊናን
ጠኔ ልትሽር ፣ሰትታትር የመንፈስ ፈውስን ልትመግብ
በአዲሱ ቀን በአዲስ መንፈስ
አዲስ አየር ልንተነፍስ ፣አዲሰ ተሥፋን ልንቀምር
እንሰ’ብሰ’ብ ከዋርካው ሥር!
ከዋርካው ስር እንታደም!
እንዲታ”ጠብ” እንዲነፃ የደም መንገድ በፍቅር ደም፡፡
….
ካየ’ን በዐይነ ልቦና ፣ ካስተዋልን በሕሊና
መጠርመር  እግር የሚጠፍ’ር ለቅን መንገድ ነው ካቴና፡፡
ፍቅርን ፈርቶ፣ብርሐን ሸሽቶ በ”እኔነት ጥግ” ከመጠ’ርነፍ
በነጠላ ከመጠ’ለፍ
ሕብረት ፈርቶ፣ ብርሐን ሸሽቶ በ”እኔነት ጎጥ” ከመኮ”ርመት
ቀና ብሎ በቅንነት፣ የወጣውን “ፀሐይ” ማየት!!

ኑ! ዋርካው ሥር እንሂድ
ድብቅ፣ሽሽግ ጥምረታችን በፍቅር ፊርማ ይውጣ ገሀድ!
በአንድ ልብ እንድንመክር ፣ በአንድ አንደበት እንድንዘምር
ከጠቢባን ከአዛውንት እግር እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር፡፡
በቅንነት እንማከር፤በቅንነት እንዋቀስ
በቅንነት እንጋሠጽ ፣ከወል ገድል እንቋደሰ
በወል ታሪክ እንዋደሥ ፤ በወል ፀፀት እንላቀስ!

ፍርሃት እንጂ ፈር ሳናጣ
ስንጨፍን ፀሐይ ስትወጣ
እግር በዝቶን ፤ መንገድ ሞልቶን
ለመራ’መድ ብልሃት ጠፍቶን
ቀን ሳይጎድለን ቅን ሰው ጎድሎ
የወል ራዕይ ፣በግል ቅዠት ተጠቅልሎ
ሕልም እያለ’ን ዒላማ አጥተን
ጥም ሲገድለን፣ ምንጮች መሀል ተጎልትን!
ቁጭት በደል ሸክም ሆኖብን፣ የኋሊዮሽ ሲጎትተን
ቋንቋ ሞልቶን፣ መግባቢያ አጥተን፣ ለወር ጉዞው ዘመን ስንሰርቅ!
እየሄድን ሳንል ፈቀቅ ፣ እየበራን ጎልተን ሳንደምቅ
ከትናንቱ ቁመት ስንደ’ቅ
ማሻ’ገሪያ ብሌን ጠቦን -ከነገ ገፅ ስንደ’በቅ
የተሥፋ አስኳል ያመቀውን ጨንግፈናል እልፍ ዕንቁላል
የከፍታ መውጫችንን ሰባብረናል ሺህ  መሰላል!
ሆኖም የእናት ምርቃቷ እርግማናችንን  ጋርዶ
አንድ አብሣሪ አይነፍገንም፣ ሲጠናብን ጽልመት ፣መርዶ!

እንሰብ’ሰብ ፣ከዋርካው ሥር በጥሞና
በአባቶች ወግ በትህትና ፣ ለመለኞች ከፍተን ጆሮ
ልቦናችን በኪዳን ቃል ተደም’ሮ፣ ፍቅር  በሕብር ተቀም’ሮ
የመጠየ’ቅ ኪን ተክነን
የመጠ’የቅ ቅን ተክነን
ጅራት ሳይሆን አከርካሪ
አእላፍ ኳክብት ሆነን መሪ
እኔነትን በእኛ ማቅለጥ
እኛነትን በእኔ ማስጌጥ ፣ለጋራ ቤት ሆነን ባለ’ጅ
ዋልታ ተክለን ዘመን ’ሚያበጅ፣ ድልድይ ሰርተን ነገር ’ሚበጅ
እንደሥልጡን ሰብዓዊ ግብር ፣ በፍቅር ጸጋ እንድን’ከብር
እንደ ጨቅሎች በንጹህ ልብ፣በሕብረ -ሕዋስ እንድንዘም’ር
ግፍን ገድፈን በምሕረት ፣ከዋርካው ሥር እንደ’መር!

እንደ’መር
ሳናንስ፣ ሳንበልጥ እንቀ’መር
ከማሕፀን፣ ከሃገር ሆድ ዕንሥ
ልጅነትን እንጠንስስ!

እስኪ ይጥናብን የትዕግሥት ኃይል፣እስቲ እንገብ’ር ለይቅርታ
ምሮ በመማ’ማ’ር ጥበብ ፣ የእስራችን ቅኔ ይፈታ!
የወጣልን ፀሐይ ሳይከስም፣በቅንነት ቀን እናክ’ም
የቅያሜን አረም ነቅለን፣ፍቅራችንን እናለምልም!!
እንጋ’መድ እን’ዋደድ፤ እንሽ’መን እንደገና
የ“እኔ” ብለን ምንገባባት ፣ወድቀንላት ምናቆማት የጋራችን ጎጆ ትዕና!
በልብ እምነት ምንሄድበት፣ የሁላችን መንገድ ይቅና!
….
ለማንነት ከጥንት ውል ድር፣በብዝኀነት ጥበብ ሕብር
እንደ’መር ፤ከዋርካው ሥር
ቁጣ፣እልህ ፣ፍርሃት ፣ በቀል
በይቅርታ እንዲቃ’ለል
ትናንትናን መሥዋእት አርገን
አንድነትን ሥንቅ አድርገን፣እንገንባ ታላቅ ነገን
እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር
በአንድ እናውጅ ተሥፋ፣ሠላም ፣ብርቱ ፍቅር
በልጅነት በደም-ሥር እስር፣በቁጭት ክንፍ በጋራ እግር
ከከፍታው የብርሃን መስክ፣ ከፍ ብለን እንድንከብር
ከሃገር ድግስ፣ ከፍቅር ዝክር፣እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር!
(ሰይፉ ወርቁ)



ባወጣው “የመደመር የግጥም ውድድር” በርካቶች  የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ የግጥም ባለሙያዎችና የሥነጽሁፍ ሃያሲያን ግጥሞቹን ገምግመው ከ1ኛ-3ኛ

የወጡትን ይፋአድርገዋል፡፡ አሸናፊዎቹም በቅርቡ በብሔራዊ ቴአትር በተካሄደ “የመደመር” እና የፍቅር የኪነጥበብ ምሽት ላይ ግጥሞቻቸውን ለታዳሚያን እያነበቡ

ሽልማቶቻቸውን ተቀብለዋል፡፡ 1ኛ የወጣው ላፕቶፕ፣ 2ኛ የወጣው ዘመናዊ ስማርት ፎን፣ 3ኛ የወጣው መለስተኛ ስማርት ፎን ተሸልመዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት

3ኛ የወጣውን ያቀረብን ሲሆን ዛሬ ደግሞ 2ኛ የወጣውን እነሆ ብለናል፡፡



ከዋርካው ሥር እንሰብሰብ
ሐገር ፍቅር ደግ’ሣ
ሽርር ጉድ’ስትል በጉጉት የልጆቿን ልብ ልታጠግብ
የሆድ ሳይሆን የሕሊናን
ጠኔ ልትሽር ፣ሰትታትር የመንፈስ ፈውስን ልትመግብ
በአዲሱ ቀን በአዲስ መንፈስ
አዲስ አየር ልንተነፍስ ፣አዲሰ ተሥፋን ልንቀምር
እንሰ’ብሰ’ብ ከዋርካው ሥር!
ከዋርካው ስር እንታደም!
እንዲታ”ጠብ” እንዲነፃ የደም መንገድ በፍቅር ደም፡፡
….
ካየ’ን በዐይነ ልቦና ፣ ካስተዋልን በሕሊና
መጠርመር  እግር የሚጠፍ’ር ለቅን መንገድ ነው ካቴና፡፡
ፍቅርን ፈርቶ፣ብርሐን ሸሽቶ በ”እኔነት ጥግ” ከመጠ’ርነፍ
በነጠላ ከመጠ’ለፍ
ሕብረት ፈርቶ፣ ብርሐን ሸሽቶ በ”እኔነት ጎጥ” ከመኮ”ርመት
ቀና ብሎ በቅንነት፣ የወጣውን “ፀሐይ” ማየት!!

ኑ! ዋርካው ሥር እንሂድ
ድብቅ፣ሽሽግ ጥምረታችን በፍቅር ፊርማ ይውጣ ገሀድ!
በአንድ ልብ እንድንመክር ፣ በአንድ አንደበት እንድንዘምር
ከጠቢባን ከአዛውንት እግር እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር፡፡
በቅንነት እንማከር፤በቅንነት እንዋቀስ
በቅንነት እንጋሠጽ ፣ከወል ገድል እንቋደሰ
በወል ታሪክ እንዋደሥ ፤ በወል ፀፀት እንላቀስ!

ፍርሃት እንጂ ፈር ሳናጣ
ስንጨፍን ፀሐይ ስትወጣ
እግር በዝቶን ፤ መንገድ ሞልቶን
ለመራ’መድ ብልሃት ጠፍቶን
ቀን ሳይጎድለን ቅን ሰው ጎድሎ
የወል ራዕይ ፣በግል ቅዠት ተጠቅልሎ
ሕልም እያለ’ን ዒላማ አጥተን
ጥም ሲገድለን፣ ምንጮች መሀል ተጎልትን!
ቁጭት በደል ሸክም ሆኖብን፣ የኋሊዮሽ ሲጎትተን
ቋንቋ ሞልቶን፣ መግባቢያ አጥተን፣ ለወር ጉዞው ዘመን ስንሰርቅ!
እየሄድን ሳንል ፈቀቅ ፣ እየበራን ጎልተን ሳንደምቅ
ከትናንቱ ቁመት ስንደ’ቅ
ማሻ’ገሪያ ብሌን ጠቦን -ከነገ ገፅ ስንደ’በቅ
የተሥፋ አስኳል ያመቀውን ጨንግፈናል እልፍ ዕንቁላል
የከፍታ መውጫችንን ሰባብረናል ሺህ  መሰላል!
ሆኖም የእናት ምርቃቷ እርግማናችንን  ጋርዶ
አንድ አብሣሪ አይነፍገንም፣ ሲጠናብን ጽልመት ፣መርዶ!

እንሰብ’ሰብ ፣ከዋርካው ሥር በጥሞና
በአባቶች ወግ በትህትና ፣ ለመለኞች ከፍተን ጆሮ
ልቦናችን በኪዳን ቃል ተደም’ሮ፣ ፍቅር  በሕብር ተቀም’ሮ
የመጠየ’ቅ ኪን ተክነን
የመጠ’የቅ ቅን ተክነን
ጅራት ሳይሆን አከርካሪ
አእላፍ ኳክብት ሆነን መሪ
እኔነትን በእኛ ማቅለጥ
እኛነትን በእኔ ማስጌጥ ፣ለጋራ ቤት ሆነን ባለ’ጅ
ዋልታ ተክለን ዘመን ’ሚያበጅ፣ ድልድይ ሰርተን ነገር ’ሚበጅ
እንደሥልጡን ሰብዓዊ ግብር ፣ በፍቅር ጸጋ እንድን’ከብር
እንደ ጨቅሎች በንጹህ ልብ፣በሕብረ -ሕዋስ እንድንዘም’ር
ግፍን ገድፈን በምሕረት ፣ከዋርካው ሥር እንደ’መር!

እንደ’መር
ሳናንስ፣ ሳንበልጥ እንቀ’መር
ከማሕፀን፣ ከሃገር ሆድ ዕንሥ
ልጅነትን እንጠንስስ!

እስኪ ይጥናብን የትዕግሥት ኃይል፣እስቲ እንገብ’ር ለይቅርታ
ምሮ በመማ’ማ’ር ጥበብ ፣ የእስራችን ቅኔ ይፈታ!
የወጣልን ፀሐይ ሳይከስም፣በቅንነት ቀን እናክ’ም
የቅያሜን አረም ነቅለን፣ፍቅራችንን እናለምልም!!
እንጋ’መድ እን’ዋደድ፤ እንሽ’መን እንደገና
የ“እኔ” ብለን ምንገባባት ፣ወድቀንላት ምናቆማት የጋራችን ጎጆ ትዕና!
በልብ እምነት ምንሄድበት፣ የሁላችን መንገድ ይቅና!
….
ለማንነት ከጥንት ውል ድር፣በብዝኀነት ጥበብ ሕብር
እንደ’መር ፤ከዋርካው ሥር
ቁጣ፣እልህ ፣ፍርሃት ፣ በቀል
በይቅርታ እንዲቃ’ለል
ትናንትናን መሥዋእት አርገን
አንድነትን ሥንቅ አድርገን፣እንገንባ ታላቅ ነገን
እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር
በአንድ እናውጅ ተሥፋ፣ሠላም ፣ብርቱ ፍቅር
በልጅነት በደም-ሥር እስር፣በቁጭት ክንፍ በጋራ እግር
ከከፍታው የብርሃን መስክ፣ ከፍ ብለን እንድንከብር
ከሃገር ድግስ፣ ከፍቅር ዝክር፣እንሰብሰብ ከዋርካው ሥር!
(ሰይፉ ወርቁ)


Read 4561 times