Wednesday, 27 February 2019 13:06

“ብር አዳዩ መሪ” መጽሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


በጋዜጠኛና ደራሲ ዘላለም መሉ የተፃፈው “ብር አዳዩ መሪ” የተሰኘ መጽሐፍ ከትላንት በስቲያ ቦሌ በሚገኘው ሬስቶራንት ተመረቀ፡፡ በምርቃት ስነ
ሥርዓቱ ላይ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ደራሲዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህርና ደራሲ አቶ
አበራ ለማ፣ በመጽሐፉ ይዘት ላይ የዳሰሳ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ከመጽሐፉ የተመረጡ ስድስት ያህል ምዕራፎችም ለታዳሚው ተነበዋል፡፡ ከዚህም ሌላ
አርቲስት ፍቃዱ ከበደን ጨምሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ደራሲና ጋዜጠኛ ዘላለም መሉ በ2003 ዓ.ም
ከዲላ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ከተመረቀ በኋላ በመምህርነት፣ በብስራት ሬዲዮና በኢቢኤስ በቴሌቪዥን በሙያው ያገለገለ ሲሆን፤
የሶማሌ ቲቪ የአማርኛ ክፍልን ለማቋቋም ወደ ጅጅጋ ከተጓዘ ጀምሮ በአካባቢው በተነሳ ብጥብጥ በሲኖትራክ ተጭኖ፣ በድሬደዋ አድርጐ አዲስ አበባ
እስከገባ ጊዜ ድረስ፣ በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ይፈጽሙ የነበሩትን ድርጊትና በርካታ ትዝብቶቹን ነው “ብር አዳዩ መሪ” በሚለው
መጽሐፉ የሚያስቃኘው፡፡ በ131 ገፆች የተነቀነበበው መጽሐፉ፤ በ98 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 741 times