Print this page
Sunday, 24 February 2019 00:00

HPV/ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ -- ለእናቶች ሰቆቃ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

የማህጸን በር ካንሰርን በሚመለከት የተለያዩ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ አቶ አወቀ ደርቤ ስለካንሰሩ ምርመራ እና ስለክትባቱ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለመዳሰስ ተያ

ያዥ በሆኑ ሐገራት የተ ደረጉ ጥናቶች ውጤትና ልምድ የሚያሳይ ጥናት ይፋ አድርገዋል፡፡ አቶ አወቀ ከአሁን ቀደም የተሰሩ ጥናቶችን ያገናዘበ እና በአሁኑ

ወቅት በምርመራውም ይሁን ክትባቱን በመስጠቱ ረገድ አስፈላጊ የሚያደርጋቸውን ነጥቦች ዘርዝረዋል፡፡
የማህጸን በር ካንሰር በእናቶች ሞት ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ነው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ /273.000/ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ወደ 83% የሚሆኑ ሴቶች ይሞታሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
99% የሚሆነው የማህጸን በር ካንሰር ምክንያት HPV/ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ የሚባለው የቫይረስ አይነት ነው፡፡
እስከአሁን በተደረገው ጥናት ወደ 150/አንድ መቶ ሀምሳ የሚጠጉ HPV/ሂዩማን ፓፒ ሎማ ቫይረሶች ያሉ ሲሆን ከ/30-40/ የሚሆኑት ግን በግብረስጋ

ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ናቸው፡፡ እነዚህ ቫይረሶች ከፍተኛና ዝቅተኛ ተብለው ይመደባሉ፡፡
HPV/ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ማለትም በወሲብ ግንኙነት በሚተላለፉት በየአመቱ በአለም ላይ ወደ /14/ሚሊየን የሚጠጉ ሴቶች በቫይረሱ በአዲስ መልክ

ይያዛሉ፡፡ ይህ ቫይረስ የያዛቸው አብዛኛዎቹ እናቶች ምንም የሚሰማቸው ሕመም ስለሌለ ብዙዎቹ ለመታከም ሳይደርሱ ለህል ፈት ይዳረጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ እድሜያቸው 15/አመት እና ከዚያ በላይ የሚሆን ወደ /29.43/ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ልጆች አሉአት ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን እነዚህም

የማህጸን በር ካንሰር ሊይዛቸው ይችላል ተብሎ የሚፈ ራላቸው ናቸው።
በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሲታይ፡-
እድሜያቸው ከ30/ አመት በላይ የሆኑ እናቶች ከሚሞቱባቸው ምክንያቶች ቀዳሚው የማህጸን በር ካንሰር ነው፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙትም በአመት ወደ /7‚600/ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ኢትዮጵያውያን እናቶች የማህጸን በር ካንሰርን ምርመራ የሚያካሂዱ ሲሆን

ከእነዚህም 6‚000/ስድስት ሺህ ያህሉ በየአመቱ እንደሚሞቱ ታውቆአል፡፡
በክሊኒኮች ተገኝተው ምርመራ የሚያደርጉትን በተመለከተ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በከተሞች የሚኖሩ እናቶች ቀደም ሲል የነበረው የመመርመር ልምድ

2.0/በመቶ ሲሆን አሁን ወደ 20.2% አድጎአል፡፡ የገጠር ነዋሪ የሆኑ እናቶች ደግሞ የማህጸን በር ካንሰርን ለማወቅ የሚያደርጉት ምርመራ 4% የነበረ

ሲሆን አሁን 14.0/% ደርሶአል።
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን ባለው ቴክኖሎጂ ምርመራውን የሚያደርጉት 0.6% ሲሆኑ ክትባትን በሚመለከት ግን አለ ወይንም የለም ለማለት የሚያስችል ይህ

ነው የሚባል መረጃ የለም አቶ አወቀ ደርቤ እንዳስነበቡት፡፡
ከላይ የተጠቀሰው መረጃ የሚያመላክተው ምንም እንኩዋን ከማህጸን በር ካንሰር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሞትና የህመም አደጋ ቢኖርም ነገሮችን ለማሻሻል

የሚያስችሉ መረጃዎች ተጠናክረው አለመገኘታቸው እና የማህጸን በር ካንሰርን ያመጣል የተባለው HPV/ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ መስፋፋት የኢትዮጵያ እናቶችን

ሰቆቃ እንደሚያበዛው እሙን ነው፡፡
ሁኔታዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የማህጸን በር ካንሰርን ለመከላከል በኢትዮጵያ ውስጥ ክትባቱ በስፋት መጀመር እንዳለበት ነው፡፡ በእርግጥ እስከዛሬ ድረስ

ጭርሱንም አልተጀመረም ማለት ሳይሆን ነገር ግን መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት መከተብ የሚችሉ ሴት ልጆች በሙሉ መከተብ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት

ከሁሉም ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚ ጠቁሙት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተጀመረው ክትባቱን የመስጠት ተግባር 90% የሚሆነውን በቫይረሱ

የመያዝ እና በማህጸን በር ካንሰር የመጎዳት እድል ይቀንሳል ተብሎ ይታመናል፡፡
አፍሪካ የተሰኘው ድረገጽ እንዳስነበበው ከሆነ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በተጀመረው የማህጸን በር ካንሰር ክትባት ዘመቻ

ወደ /1.1/ ሚሊዮን የሚሆኑ የኢትዮጵያ ልጃገረዶች ክትባቱን እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡ ክትባቱ የሚፈቀደው የግብረስጋ ግንኙነት ላልፈጸሙ

ልጃገረዶች ነው፡፡ እድሜያቸው ገና ልጅ የሆኑ ሴቶች በአንዳ ንድ ምክንያት ሳያስተውሉ ለሚከተሉት ችግሮች ሊዳረጉ ስለሚችሉም ለጤናቸው አስቀድሞ መጠንቀቅ

ስለሚያስፈልግ ክትባቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው፡፡   
እድሜያቸው ገና ወጣት የሆኑ ሴት ልጆች ለወሲብ ግንኙነት ሳይደርሱ ወሲብ መፈጸም ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡
ጥንቃቄውን ለማድረግ ገና እድሜያቸው ባልፈቀደበት ወቅት የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ መጀመር ብቻም ሳይሆን ከተለያዩ ወንዶች ጋር ግንኙነቱን ሊፈጽሙ

ይችላሉ፡፡
በሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ሳቢያም ለኤችአይቪ ቫይረስ የመጋለጥ አደጋው ሊኖር ይችላል፡፡
ስለዚህ እነዚህ ልጃገረዶች ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ለማህጸን በር ካንሰር እንዳይዳርጋቸው ክትባቱ መከላከያ እንደሚ ሆናቸው እርግጥ ነው፡፡ ይህ በፈረንጆቹ

ቀን አቆጣጠር 2018/ ማብ ቂያና 2019/ መጀመሪያ ተግባር ላይ የዋለው ክትባትን ለልጃገረዶቹ የማዳረስ ዘመቻ በኢት ዮጵያ ያለውን በካንሰሩ የመያዝ

እድል እጅግ እንደሚቀንሰው እሙን ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት እንደገለጸውም በአፍሪካ ሴቶች በየአመቱ ወደ /68.000/ ከ HPV ጋር በተያያዘ ለሕ

ክምና ይቀርባሉ፡፡ ይህም ሙሉ ለሙሉ ሁሉንም የሚመለከት መረጃ ይሆናል ተብሎ የማይገመ ትበት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተጠቁሞአል፡፡ በየጤና

ተቋሙ ያለ የመረጃ አያ ያዝ ጉዳይ እንዲሁም ታካሚዎች በትክክል ወደ ተቋም ያለመቅረብ ጉዳይ የመሳሰሉት ነገሮች መረጃውን ትክክለኛ ላያሰኙት ይችላሉ ይላል

ድረገጹ፡፡ ባጠቃላይም፡-
በአፍሪካ የማህጸን በር ካንሰርን በሚመለከት ከ/100.000/ሴቶች 34/የሚሆኑት ለምርመራ ይቀርባሉ፡፡
ከ100.00/ሴቶች 23/ሀያ ሶስቱ በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት በየአመቱ የሚሞቱባት አህጉር ነች አፍሪካ፡፡ እንደ አፍሪከ ድረገጽ፡፡
HPV የተሰኘው ቫይረስ ቁጥር በርከት ያለ ቢሆንም የማህጸን በር ካንሰር ቫይረስን በሚመለከት በከፍተኛ ደረጃ ጎጂ ተብለው የተፈረጁት ቁጥር /16/ እና

/18/ ናቸው፡፡
የተለያዩ አጥኚዎች እንደገለጹት በአፍሪካ ቁጥር/16/ እና /18/ በተባሉት ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረሶች 45.1% ያህል ሴቶች ተይዘዋል፡፡
ሌሎች አጥኚዎች ደግሞ እንደሚመሰክሩት በተለያዩ ሀገራት HPV በተመለከተ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሚያመላክቱት ሴቶች በአለም ዙሪያ ምን ያህል እየተጎዱ

መሆኑን ነው፡፡
HPV 16/18 በተባለው ቫይረስ ምክንያት የማህጸን በር ካንሰር የተያዙ እስራኤላውያን 60%፤ 87.5 % በሴንትራል እና ምስራቅ አውሮፓ ፤80%

በኢንድያ መመዝገባቸውን የአቶ አወቀ ደርቤ ጥናት ያሳያል፡፡    
ወደኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመለስ በተለይም HPV /16-18/ እና በተጨማሪም HPV 52/ ሴቶቹ የማህጸን በር ካንሰር የሚያዙባቸው ዋናዎቹ ቫይረሶች

ስለሆኑ አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ክትባት መስጠቱ ላይ ትኩረት ማድረግ ትክክለኛው ውሳኔ ነው፡፡ የተገኙት አሀዞች በትክክል በአገሪቱ ውስጥ ያለውን

ሁኔታ የሚያሳዩ ናቸው ማለት ስለማይቻልም ቀጣይነት ያለው ጥናት በየመስተዳድሩ ባሉ የሚመለከታቸው አካላት ቢደረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው የሚል እምነት

አለ፡፡ከዚህ በተጨማሪ እናቶች የሙያ አካላት በሚሰጡት ምክር መሰረት አስቀድሞ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ 29.43/ሚሊዮን እድሜያቸው አስራ አምስትና ከዚያ በላይ የሆኑ የማህጸን በር ካንሰር ተጎጂዎች ሊሆኑ የሚችሉ
KEY WORDS:
ሴቶች የሚኖሩባት አገር ናት፡፡ ስለዚህም ክትባቱን ለሁሉም ሴት ልጆች ማዳረስ ቅድሚያን የሚሻ ሲሆን ድርሻውን ቤተሰብም ሊጋራው ይገባል የአቶ አወቀ

ደርቤ ጥናት እንደሚያሳየው፡፡

Read 6982 times