Sunday, 10 March 2019 00:00

እነ አቶ ማሙሸት አማረና የቀድሞ የመኢአድ አመራሮች ወደ ፓርቲያቸው ሊመለሱ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)


የቀድሞ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረን ጨምሮ በተለያዩ አለመግባባቶች ከፓርቲው ወጥተው የነበሩ አመራሮች እርቅ ፈፅመው ወደ ፓርቲው ሊመለሱ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ለረጅም ጊዜያት እርቅና ድርድር ሲካሄድ መቆየቱን ለአዲስ አድማስ የጠቆሙት ምንጮች፤ በአሁኑ ወቅት ከእነ አቶ ማሙሸት አማረ ጋር በአብዛኞቹ ችግሮችና የግጭት ምክንያቶች ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ የእርቅ ማብሰሪያ ቀን እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ከድርጅቱ በተለያየ ጊዜ በተፈጠሩ የአመራር ውዝግቦች ተሰናብተው የነበሩ ከ60 በላይ አመራር አባላት በዚህ እርቅ ወደ ፓርቲው በድጋሚ እንደሚመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የፓርቲው አመራሮች እና እነ አቶ ማሙሸት ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የእርስ በእርስ ምክክር አድርገው የእርቅ ውሣኔ ላይ መድረሳቸውን ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የፓርቲው አመራሮች፤ ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ለመገናኛ ብዙኃን ይገለፃል ብለዋል፡፡
የቀድሞ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ማሙሸት አማረ፤ በሽብርተኝነት ታስረው ከወራት በፊት ከእስር መለቀቃቸው ይታወቃል፡፡  

Read 762 times