Print this page
Sunday, 10 March 2019 00:00

ጠ/ሚኒስትሩ ከግል የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ይወያያሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

እጣ የወጣባቸው የኮዬ ፈጬ ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተለለፉ ክልሉ አገደ


ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ ከሚገኙ ሁሉም የግል ሚዲያ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ዋና አዘጋጆች እንዲሁም ጋዜጠኞች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በነገው ዕለት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ይወያያሉ፡፡
ሁሉም የግል የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎችና አመራሮች እንዲሁም አዘጋጆች በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን የገለፀው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቢሮ፤ እያንዳንዱ የሚዲያ ተቋም ስራ አስኪያጁንና ዋና አዘጋጁን ጨምሮ አምስት ተወካዮች ይሳተፋሉ፡፡
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ መምህራንና አርቲስቶችን ጨምሮ ከተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር የሚደረገው የነገው ውይይት የመጀመሪያው ይሆናል ተብሏል፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በዋናነት በሃገሪቱ ሚዲያ ላይ ባሉ ተግዳሮቶች፣ ጋዜጠኞች በሚገጥሟቸው ፈተና እና ለወደፊት ሚዲያን አስመልክቶ በመንግስት በተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሏል፡፡ የውይይቱ ዋነኛ ትኩረትም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ ጫናዎች እየተመናመነ የመጣውና ህልውናው ለአደጋ የተጋለጠው የህትመት ኢንዲስትሪው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባለፉት 27 ዓመታት የሚዲያ ባለሙያዎች በጠ/ሚኒስትር ደረጃ የመወያየት የመመካከር ዕድል አላገኙም፡፡
የሃገሪቱን ሚዲያዎች ለማጠናከር መንግስት ስለያዘው እቅድም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


Read 6573 times