Print this page
Saturday, 09 March 2019 00:00

አንጋፋውን የግብርና ሳይንቲስት የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ተወዳጅ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኢንተርፕራይዝ፤ በእውቁና አንጋፋው የግብርና ሳይንቲስት ዶ/ር ስሜ ደበላ ስራና ህይወት ላይ የሚያጠነጥነውን የ54 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር የዶክተሩ ቤተሰቦች፣ የግብርና ሚኒስቴር ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት በቪዲዮ በኦዲዮ ይመረቃል ተብሏል፡፡
ዘጋቢ ፊልሙ በዋናነት የሳይንቲስቱን የልጅነት፣ የስራና የትምህርት ጊዜ የሚዘክር ሲሆን በ2010 ዓ.ም ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ስራዎቻቸውንና ታሪኮችን በቪዲዮ ቀርፆ የማስቀመጥ ልምድ ስለነበራቸው እነዚህ መረጃዎች በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ተካትተው ስራውን አበልጽገውታል፡፡ ከ41 ዓመት በፊት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ም/ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ስሜ፤ የግብርና ምርምር ላይ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ፣ የምርምር ተቋሙ አንዱን ህንፃ በስማቸው መሰየሙም ተገልጿል፡፡
ይህንን ሁሉ የሚዘክረው ዘጋቢ ፊልም ምርቃት ላይ ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉም ተብሏል፡፡ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ታላላቅ የሀገር ባለውለታዎችን ታሪክ በዘጋቢ ፊልም በማቅረብ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡

Read 697 times