Print this page
Saturday, 09 March 2019 00:00

የደራሲ ለማ ደገፋ 6 መጽሐፎች ዛሬ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የደራሲ ለማ ደገፉ ስድስት መጽሐፎች ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ይመረቃል፡፡
መጽሐፎቹ በአማርኛ፣ ኦሮሚያኛና እንግሊዝኛ የተፃፉ ሲሆኑ በአመራርነት፣ በልጅና በቤተሰብ ግንባታ፣ በማህበራዊ ጉዳዮችና በስልጠና ላይ ያተኩራሉ፡፡ “ካሳደጉ አይቀር”፣ “ካደጉ አይቀር”፣ “Leading”፣ “ኡሊቃጀላ”፣ “መልአኩ” እና “ቀጥተኛው በትር” የተሰኙት መጽሐፎች አገርን፣ አመራርንና ማህበረሰብን በማንቃትና በማሳደግ ደረጃ ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
አቶ ለማ ደገፉ “የአይሶል” ቢዝነስና ስራ አመራር አማካሪ ድርጅት መስራችና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ የተለያዩ ባንኮችና ኢንሹራንሶችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የመንግስት መስሪያ ቤት አመራሮችን በአመራርና በቢዝነስ ዙሪያ ያማክራሉ፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም በዚሁ ሀሳብ ላይ የሚያጠነጥኑ 10 መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በማግኖሊያ ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

Read 1158 times