Sunday, 10 March 2019 00:00

“የብሔርተኞች የትድግና ጉዞ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በዶ/ር አንድነት ቶኩማ የተፃፈውና የአገራችንን የረጅም ጊዜ የፖለቲካና የታሪክ ጉዞ ከብሔርተኞች ትግልና ሚና አንፃር የሚተርከው “የብሔርተኞች
የትድግና ጉዞ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ጸሃፊው “የአማራ ህዝብን ትግል እንደ ናሙና” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር ኢዴፓ፣ መአህድ፣ አዴሀን፣ በጠቋር ብሔርተኞች ፊት የቆሙ የትድግና ክስተቶች ወይስ ምትሀቶች በማለት የእነዚህን ድርጅቶች አካሄድና ምግባርም ይተነትናል፡፡
     በተለይ አማራው በአገር ምስረታና ግንባታው ውስጥ የነበረውን የማይተካ ሚናና ኃላፊነት፣ ከህዝቡ ታሪክና ስነ ልቦና አንፃር በማየት ህዝቡ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ፖለቲካና ሌሎች አገራዊ ተሳትፎዎች ያለውን ድርሻና ሚና ይፈትሻል፡፡ በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ የአማራ ህዝብ ደርሶበታል ያለውን በደልና ግፍ በማስረጃና በታሪክ ጥቁምታ እያጣቀሰ የሚተነትነው መፅሐፉ፤ በ352 ገጾች ተቀንብቦ በ200 ብር፣ በ20 ዶላርና በ15 የእንግሊዝ ፓውንድ ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 199 times