Sunday, 10 March 2019 00:00

“እሪ በከንቱ” የግጥም መጽሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


         የዳንኤል ታረቀኝ የግጥም ስብስቦች ያካተተው “እሪ በከንቱ” የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከትላንት በስቲያ በደብረ ዳሞ ሆቴል ተመረቀ፡፡ ማህበራዊ ትዝብቶችን፣ ወቅታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያንፀባርቁ 65 ያህል ግጥሞችን የያዘው መጽሐፉ፤ በ84 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ገጣሚው የግጥሙን ርዕስ “እሪ በከንቱ” ያለበት ምክንያት በተለምዶ እሪ በከንቱ የተሰኘው ሰፈር ውስጥ ተወልዶ ያደገ ሰፈሩ ለመልሶ ልማት ከፈረሱት የአዲስ አበባ አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ፣ ከዚያ የተነሱ ማህበረሰቦችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍልሰት ለማስታወስ እንደሆነም በምርቃት ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ገልጿል፡፡

Read 4720 times