Sunday, 17 March 2019 00:00

“ሰፈረ ጐድጓዳ” አዲስ ሙዚቃዊ ቴአትር ለእይታ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


       በደራሲ ማረኝ ኃ/ማርያም ተደርሶ በአርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ የተዘጋጀው “ሰፈረ ጐድጓዳ” ሙዚቃዊ ቴአትር ባለፈው ረቡዕ ተመርቆ ለእይታ ቀረበ፡፡ በሰላምና መቻቻል ላይ ትኩረቱን አድርጐ የተዘጋጀውና ሁለት ጐራ ለይተው ሲናቆሩ የነበሩ ወገኖችን ታሪክ የሚዳስሰው ቴአትሩ በመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች በሚያስማሟቸው ተስማምተውና ልዩነታቸውን አክብረው ወደመኖር ሲሸጋገሩ ያሳያል ተብሏል፡፡
በዚህ የሙሉ ሰዓት ቴአትር ላይ መሐተመ ሀይሌ፣ ወንድወሰን አውራሪስ፣ ደመወዝ ጌታነህ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ማረኝ ኃ/ማርያም ማንአይቶሽ አበበ፣ ዳዊት መኩሪያ፣ ትዕግስት ሰለሞን፣ ሃና ብርሃኑ፣ ሚኪያስ ልዑልሰገድ፣ ኤርሚያስ ወርቁ፣ አወቀ ቀለሙ ፍቅር አበራ፣ የማታወርቅ ብርሃኑ፣ ፍሬ ጨርግድና ገዛኸኝ ማሞ የተወኑበት ሲሆን፤ ቴአትሩ ዘወትር ረቡዕ ከ11፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለእይታ እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡

Read 4459 times