የገጣሚ አሸናፊ ጌታህ (ዲያቆን) “ላንቺ ሲሆንማ” የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በአቤል ሲኒማ ይመረቃል፡፡ በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ በርካታ የኪነ ጥበብ ሰዎችና እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ አፈወርቅ በቀለ፣ መምህር መሰረት አበጀ፣ ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ ገጣሚና ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ፣ የሙዚቃ ተመራማሪ ሰርፀፍሬ ስብሃትና ሌሎችም አንጋፋን ወጣት ከያኒያን በአኬቡላንስ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና በመፅሐፉ ላይ እንደሚወያዩ ታውቋል፡፡