Sunday, 31 March 2019 00:00

የሚሼል ኦባማ መጽሃፍ በሽያጭ ክብረወሰን ሊያስመዘገብ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 “ቢካሚንግ” የሚል ርዕስ ያለውና በቀድሞዋ የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ የተጻፈው ተወዳጅ መጽሃፍ በአለማችን የግለታሪክ ማስታወሻ መጽሃፍት ሽያጭ ታሪክ ክብረወሰን ሊያስመዘገብ መቃረቡን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
በወረቀት፣ በሶፍት ኮፒና በድምጽ ቅጂ በአለም አቀፍ ደረጃ 10 ሚሊዮን ኮፒዎች የተሸጡለትና በአለማችን የግለታሪክ ማስታወሻ መጽሃፍት ታሪክ ክብረወሰን ለማስመዝገብ የተቃረበው መጽሃፉ፣ ባለፈው ህዳር ወር ላይ ለህትመት የበቃውና በሰሜን አሜሪካ ብቻ በአንድ ቀን ውስጥ 725 ሺህ ኮፒዎች፣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ደግሞ 2 ሚሊዮን ኮፒዎች እንደተሸጠ ዘገባው አስታውሷል፡፡
በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጅነትን ያተረፈው “ቢካሚንግ” በታተመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአመቱ ከፍተኛ ሽያጭ ካስመዘገቡ መጽሃፍት ተርታ ለመሰለፍ መቻሉንም፣ መጽሃፉ ከ6.2 ሚሊዮን ኮፒ በላይ ከተሸጠበት አሜሪካ ባለፈ እንግሊዝና ጀርመንን ጨምሮ በሌሎች አገራትም በከፍተኛ ሽያጭ ክብረወሰን ማስመዝገቡን ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 7047 times