Saturday, 06 April 2019 15:02

በትግራይ በሺዎች የሚቆጠሩ “ህገ ወጥ” የተባሉ ቤቶች በኃይል እየፈረሱ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)


በትግራይ ክልል መቀሌን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች “ህገ ወጥ” የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ለከፋ ሰብአዊ ጉዳት መጋለጣቸው እንዲሁም ድርጊን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች መበራከታቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ በበኩሉ መንግስት እርምጃውን በድጋሚ እንዲያጤን ጠይቋል፤ የድሃን ቤት ህገ ወጥ በሚል ማፍረስ እንደማይገባም አሳስቧል፡፡
ቀደም ባለው ሳምንት በመቀሉ ዙሪያ በተለይም ደብሪ እና ደንጉር በተባሉ አካባቢዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ህገ ወጥ ናቸው በሚል በቡልዶዘር በመታገዝ መፍረሳቸውን እንዲሁም በአዲራት ከ240 በላይ ቤቶች በዚህ ዘመፋ መፍረሳቸውንና ማይ መሳኒ በተባለ አካባም ከ1000 በላይ ቤቶች ምልክት ተደርጎባቸው የማፍረሱ ተግባር እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
በዛላምበሳ እና በሽሬ ከተሞችም በተመሳሳይ ህገ ወጥ የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች በርካታ አባወራዎች ቤት አልባ ሆነው ሜዳ ላይ ወድቀው ለከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት መዳረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ይህን ህገ ወጥ የተባሉ ቤቶችን በሃይል በቡልዶዘር በመታገዝ የማፍረስ ዘመቻን ተከትሎም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች በየጊዜው እየተካሄዱ መሆኑን የገለፁት የአረና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገ/ሥላሴ በበኩላቸው መንግስት ህዝቡን ለሰብአዊ ጉዳት ከመዳረግ መታቀብ አለበት ብለዋል፡፡
ፓርቲያቸው በበኩሉ ህገ ወጥ ግንታ አስቀድሞ ማስቆም ባልተቻለበት ሁኔታ ዜጎች ሃታቸውን ላባቸውን አፍሰው ከሰሩ በኋ ማፍረስ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ነው ብሏል፡፡ በዚህም የክልሉ መንግሰት ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያጤን ጠይቋል አረና፡፡
በሌላ በኩል ነባር የመሬት ይዞታቸውን በማጣታቸው የተነሳ አማከለች ይሞሐር የተባሉ እናት ራሳቸውን አጥፍተው መሞታቸውን እንዲሁም በተመሳሳይ ቤታቸው የፈረሰባቸው ፀለላ አብረሃ የተባሉ እናት በቅፅበታዊ ህመም ህይወታቸው ማለፉን ምንጮች አስታውቀ

Read 7240 times