Saturday, 06 April 2019 15:29

“የመንጌ ውሽሚት” ለ3ኛ ጊዜ ለንባብ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


የደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ አለነ ሥራ የሆነው “የመንጌ ውሽሚት” መፅሐፍ ለ3ኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በ2005 ዓ.ም በዚህ ወር ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ የበቃው በወቅቱ እጅግ ተነባቢነትን ያተረፈው ይሄው መፅሐፍ ጣፋጭ የልጅነት ታሪኮችን የያዘ ሲሆን፤ በመፅሐፉ ላይ አስተያየት የሰጠው የ“ፒያሳ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ” መፅሐፍ ደራሲ ጋዜጠኛ መሀመድ ሰልማንም “እንደ ናና ከረሜላ የሚጣፍጡ ታሪኮች” ብሎት ነበር፡፡ ይሄው በ288 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ  ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ ታትሞ በ120 ብር ገበያ ላይ መዋሉን ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ አለነ ገልጿል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “እንክልካይ” እና “effective English” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱም አይዘነጋም፡፡

Read 6402 times