(የተዋነይ ዘጎንጅ "ሙሴ እግዚአብሄርን ፈጠረ" ቅኔያዊ ግጥም )
ግጥምበቋንቋ “ውብድርደራ ”እናበሀሳብ “ስሜትነኪ”ቅመራየተመጠነእምቅአሰነኛኘትነው፡፡ኪናዊነቱአእምሮን፣ልብንናልቦናንመቀተሩላይነው፡፡ቅተራውከልማድመሻገሩነው፡፡ይህደግሞበዘይቤው፣በምሰላው፣በጥልቀቱ፣በውስብስብነቱናበረቀቀውበቱይገለፃል፡፡ውበቱንለመግለፅይመስለኛል፣ፉለር፤ " ግጥምበንግግርየሚገለፅሙዚቃነው፤ሙዚቃደግሞበድምፅየምትገለፅግጥምናት " የሚለን.... ግጥምምሆነሙዚቃመሰረታቸውድምፅነው፡፡የድምፅኪናዊውህደትበምጣኔተሞሽሮሲቀርብልከኛምትይፈጥራል፡፡የተመጠነምትደግሞውብሙዚቃንይፈጥራል፡፡ለዚህነው "ፉለር" ሙዚቃንናግጥምንበድምፅያዋሃዳቸው፡፡ሁለቱምለመደመጥየሚከወኑጥበቦችናቸው፡፡
በድምፅህልውናይቋጠራል፡፡ስውሩግልጥይሆናል፡፡ድምፅረቂቅበመሆኑለነፍስይቀርባል፡፡የግጥምሆነየሙዚቃሀይልምንጭይኸውነው፤ለልብስለሚቀመሩ፡፡
በግጥምሁሉነገራችንንእንቋጥራለን፡፡ስርዓትእንመረምራለን፡፡የጎደለንንእናሟላለን፡፡የማያስፈልገንንእንገፋለን፤ " ስነግጥምየገዛራሱህይወትሒስነው" እንዲሉየስነግጥምሊቃውንት፡፡ሒሱበየትኛውምመንገድ፣ለየትኛውምአካልሊሰነዘርይችላል፡፡ለአብነት፦
እራቤ፣ጥማቴ፣እርዛቴሦስቱ፤
ይደበድቡኛልባንድእየዶለቱ፡፡
እግዜርምእንደሰውባሰትእየማለ፣
አንድእንጀራብለውሙትየለኝምአለ፡፡
ጠኔበርትቶመፈናፈኛስናጣእግዜርንእንማጠናለን፡፡ያምሆኖምላሽስናጣ " የለህማከመንበርህ"ንእናንጎራጉራለን፡፡የስሜቱብርታትእረፍትይነሳል፡፡ለዚህመሰለኝ " ግጥምየብርቱስሜትመግለጫነው" የሚባለው፡፡የሚንተከተክ፣የሚቃትትናቀትሮየሚይዝስሜትይገለፅበታል፡፡ስለሆነምግጥምቀታሪነው፡፡
[ቀታሪ÷ስሩቀተረነው፡፡ቀተረ÷እኩልለመሆንተከታተለ÷ተቀታተረ÷ተመለካከተ÷ተወዳደረ÷ተተካከለ÷ተመዛዘነ÷ተፈካከረ÷ተፈላለገ (አስ) ከባለቀትርአትቀታተር፡፡( ከሣቴብርሃንተሠማ÷የዐማርኛመዝገበቃላት÷ገፅ፫፻፹፬÷2008 ዓ.ም ) ግጥምምንጬህይወትነውና (ቋንቋው(መንገዱ) አዕምሮን፣ስሜቱልብንእናመልዕክቱልቦናንይቀትራል፡፡) አዕምሮን፣ልቦናንናልብንየቀተረከምናብየሚፈለቀቅየፀነነየጥበብውጤትነው፡፡መቀተሩከልማድጋርየሚደረግግብግብነው፡፡ፈጠራደግሞልማድንመሻገርይጠይቃል፡፡ከልማድያልተሻገረግጥምነፃአያወጣም፡፡አይታኘክም-የተመጠጠነውና፡፡]
* * * ቁጥር 6
[ይህየተዋነይዘጎንጅቅኔነው፡፡ ካየኋቸውትርጉሞችሁሉየተሻለስለሆነመርጨዋለሁ፡፡]
'ሰውልጅበገዛ'ጁ፥ላስቀመጠውፈጥሮ
ይገዛልበአንክሮ
ሰውፈርቶእንዲገዛ፥እንዲሰላኑሮ
ለዚኽምማስረጃውየሙሴነገርነውአምላኩንመፍጠሩ
አምላኩምመልሶ፥እሱኑፈጠረውበአምሳሉበግብሩ
(ኀሠሣ፣ሕይወትተፈራ፣2009 ዓ.ም፣ገፅ132 ) (ሕይወትታደሰእንደተረጎመችው)
በግጥሙበርካታሀሳቦችተነባብረዋል፡፡በመጀመሪያውአርኬየሰውልጅኑሮይሰምርዘንድለማህበራዊህይወቱህግሰራ፣ቀኖናአስቀመጠ፡፡ለነገሮችመመዘኛመስፈርትቀመረ፡፡በተጨማሪምየሰውልጅለግንዛቤ፣ለአረዳድይመችዘንድቅርፅአስያዘ፣አስተዋወቀ፣በሚስማማውመንገድውስጡንገለፀወይምፈጠረየሚለውተጠቃሽነው፡፡
በሁለተኛውአርኬ "ሙሴእግዜርንፈጠረ " የሚለውዋናጉዳይሲሆንበአምሳሉበግብሩፈጣሪንፈጠረው፣አስተዋወቀው፣ለአእምሮምስልሰጠ፣ቅርፅአስያዘ፣ለመለኮታዊሀይልያለውንግንዛቤእንረዳዘንድገለጠየሚልሲሆንበሌላመልኩደግሞሙሴህልውያልሆነውንእግዚአብሄርፈጠረ፡፡ግብር፣ምግባርናህልውናአላበሰው፡፡በሌለነገርላይስርዓት፣ህግናቀኖናዘረጋ፡፡
በሌላመልኩየሰውልጅባምሳሉናበግብሩእግዜርንእየፈጠረአመለከ፡፡ለፍላጎቱተገዥሆነ፡፡እራሱላረቀቀውቀኖናኖረ፡፡ተማረከ፣እጅሰጠ፡፡የሰብዕና፣ልዕልናመስፈሪያአደረገው፡፡በዚህምምክንያትእራሱንዳግምፈጠረ፡፡ልዕልናተጎናፀፈ፡፡ከሀጢያትነፃ፡፡የፍጥረትአለቃሆነ፡፡እራሱንሾመ፡፡እዚህላይየሰይፉመታፈሪያፍሬውንግጥምማስታወስግድይለናል፡፡እነሆ፦
ሰው
የሴሎችሴሎችክምችት
የቃላትርችት፦--
ጭንቅላታም፣
በባሰይባስዐይነቱነገርያዢ
ፍጥረትንገዢ
ሳያሠልስ
እሱውአንጋሽእሱውንጉሥ፡፡
(ውስጠት፣ሰይፉመታፈሪያፍሬው፣፲፱፻፹፩፣ገፅ 78)
"መራጭምአስመራጭምእሱው" ያለይመስለኛል፤የሁሉጌታ --ሰው፡፡
በሌላበኩልደግሞበምድርላይየሃይማኖቶችመበርከትምሆነመስፋፋትምክንያቱሰውበሚፈልገውመንገድአምላኩንመፍጠሩነው፡፡ለዚህምእንደምክንያትየሚጠቀሰውደግሞየገደብየለሽፀጋዎችባለቤትመሆኑነው፡፡ገደብየለሽፀጋዎቹንቃቱንይወስናሉ፡፡ለዚህምመሰለኝእየሱስበምድርላይሁሉንምየሰውልጅማሳመንያልቻለው፡፡
በተጨማሪምየሰውልጅበምኞትሰከረ፡፡ህግምአወጣ፡፡ህጉቀኖናሆነናእራሱንፈጠረው፡፡ለመንፃት (ለመመረጥ) ያስቀመጠውንመስፈርትለማሟላትታተረ፣ደከመ፡፡የተሳካለትተመረጠ -- በሰው፡፡ያልተሳካለትተገፋ(ሀጢያተኛሆነ)፡፡ያምሆኖ "ኑሰውንባምሳላችንእንፍጠር" የሚለውአባባልለሙሴምይሰራል፡፡የሰውልጅም "ኑእግዜርንባምሳላችንእንፍጠር " ያለይመስለኛል፡፡
በርግጥግጥሙየሰውንልጅመለኮታዊምልከታእንጂ "በራሱ" የእግዚአብሔርንአለመኖርየሚያረጋግጥአይደለም፡፡ግጥሙየጎደለንንየሚሞላ "መንፈሳዊ " ሰነድነው፡፡የጋራምሰሶለማቆምየሚደረገውንጥረትከማሳየትባሻገርህይወትምልከታእንደሆነችምይጠቁማል፡፡
ግጥሙቅኔያዊበመሆኑየትየለሌፍቺተሸክሟል፡፡ልክእንደሽንኩርትነው፡፡ያመልማሎያህልየተንዠረገገ፡፡ውበቱያማልላል፡፡ስሜቱቁዘማነው፡፡ያብከነክናል፡፡ቀታሪነው፡፡የህይወትሒስበመሆኑብዙቀዳዳይሞላል፡፡ዜማዊከሚባለውየግጥምዓይነትየሚመደብነው፡፡
"ሙሴሕዝቡበህግይገዛዘንድፈጣሪንፈጠረ፡፡ፈጣሪምሙሴንፈጠረ" እንዲሉ፣ " እኛምበህግእንገዛዘንድስነግጥምንፈጠርን፡፡ስነግጥምደግሞእኛንፈጠረ፡፡"
****
ከአዘጋጁ፡- ጸሃፊውን በኢሜይል አድራሻው፡-
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ማግኘት ይቻላል፡፡
Saturday, 06 April 2019 15:45
ቀታሪ ግጥም
Written by ከአንለይ ጥላሁን ምትኩ
Published in
ጥበብ