Saturday, 13 April 2019 13:52

ሁለት መንፈሳዊ መፅሐፎች ነገ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በዳዊት አብረሃም የተሰናዱትና በመንፈሳዊ አስተምህሮ ላይ የሚያተኩሩት “ዕቅበተ እምነት በእንተ ነገረ ድኅነት” እና “ኦርቶዶክሳዊ ሥነ - ሰብእ” የተሰኙት መፅሀፍት ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ ይመረቃሉ፡፡ በመፅሀፍቱ ይዘት ላይ ትምህርትና ዳሰሳ
በሊቃውንት እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡ “ዕቅበተ እምነት በእንተ ነገረ ድኃነት የተሰኘው መፅሀፍ በተለይም የፖፕ ሺኖዳ ሳልሳዊ ትምህርቶችን መነሻ አድርጎ፣ በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን ምንጮች የዳበረና በመፅሀፍ ቅዱሳዊ ዐውድ የተሰናዳ መሆኑን ፀሐፊው የገለፁ ሲሆን፣ በ264 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ120 ብርና በ30 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ “ኦርቶዶክሳዊ ሥነ - ሰብዕ” የተሰኘው መፅሀፍ ደግሞ በሀይማኖቱ አስተምህሮና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በ13 ምዕራፍና
በ130 ገፆች ተመጥኖ በ40 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 974 times