Saturday, 13 April 2019 13:50

“The big Art Sale” የሥዕል አውደርዕይ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ዋትስ አውት ኦምኒ ሚዲያ ከሂልተን አዲስ አበባ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት “The Big Art Sale” የስዕል አውደ ርዕይ ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ ምሽቱ 12፡00 እንደሚቆይ አዘጋጆቹ ከትላንት በስቲያ ረፋድ ላይ በሂልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ ከመቶ በላይ ኢትዮጵየውያን ወጣትና አንጋፋ ሰዓሊያን ስራዎቻቸውን ለእይታ የሚያበቁ ሲሆን ሰዓሊያንና የጥበቡ አፍቃሪያን ተገናኝተው ስለ
ሥዕል ይወያያሉ ይገበያያሉም ተብሏል፡፡ ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ የስዕል አውደ ርዕይ ላይ ቤተሰቦች በጋራ የሚዝናኑበት ለማድረግ የምግብ የመጠጥ፣ የሙዚቃና የህፃናት መጫወቻ ፕሮግራም ጎን ለጎን የሚዘጋጅ ሲሆን ለህፃናት አይስክሬምና መላ ቤተሰቡን የሚያሳትፉና የሚያዝናኑ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡

Read 888 times