Print this page
Saturday, 13 April 2019 13:53

“ኢትዮ አዲስ የፋሲካ ባዛር” ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 እነዳዊት መለሰ፣ ሸዋንዳኝ ሃይሉ፣ ሳሚዳን ያቀነቅናሉ

           በጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘርስ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተውና በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት “ኢትዮ አዲስ የፋሲካ ባዛር” ዛሬ ረፋድ 4፡00 ላይ በልዩ የመዝናኛ ስነ ስርዓት በይፋ ይከፈታል፡፡ በባዛሩ እንደነ ዳዊት መለሰ፣ ሸዋንዳኝ ሀይሉ፣ ሳሚ ዳን፣ እሱባለው ይታየው፣ ኤፍሬም አማረ፣ ቸሊና፣ እጊቱ፣ ሌንጮ (አብዲሽኩር) አነጋጋሪው አብርሃም (የኔ ቆንጆ ኑሪ)፣ መሳይ ተፈራ፣ ጆርዳንና ቢ-ግዕዝ እንዲሁም በርካታ ድምፃዊያን ከ4 በላይ በሆኑ ምርጥ ባንዶችና ስመ ጥር ዲጄዎች እየታገዙ ስራቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
ከ900 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኙበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ባዛር ጥራት ያላቸው በርካታ አይነት እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙበት ከመሆኑም ባሻገር በርካታ የመዝናኛ ፕሮግራሞችም ይካሄዱበታል፡፡ በተጨማሪም እውቅ ሰዓሊያን የሚሳተፉበትና ለ15 ቀናት የሚቆይ የስዕል አውደርዕይ ማዘጋጀቱንም የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ታደሰ ታምራት አስታውቋል፡፡ በዓሉን አስመልክቶ የባህል አልባሳትን ትኩረት ያደረገ ትርኢትና የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ለታዳሚው በየቀኑ እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
ከውስጥ ምንጮች በደረሰን መረጃ፣ የፋሲካ ዋዜማ ዕለት ትልቅ የባዛሩ መዝጊያ ኮንሰርት የሚዘጋጅ ሲሆን በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት እንደሚተላለፍም ታውቋል፡፡

Read 2367 times