ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በሀሰን ኡመር አብደላ “ከጦቢያ ዘመን ተሻጋሪ መጣጥፎች” መፅሀፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ - መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ (ወመዘክር) ውይይት ይካሄዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሶሲዮሎጂ መምህር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ውብሸት ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ የገለፀው ሚዩዚክ ሜይዴይ፤ ፍላጎት ያለው በውይይቱ እንዲሳተፍ ጋብዟል፡፡