Saturday, 20 April 2019 14:04

4ኛው ዙር ጎህ የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

4ኛው ዙር ጎህ የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በምሽቱ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ በሀይሉ ገ/እግዚአብሔርና ጋዜጠኛ ፅጌረዳ ጎንፋ ወግ የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ ናትናኤል ጌቱ፣ ኤልያስ ሽታሁን፣ ደስታ ነጋሽ፣ ልሳን ሀጎስ፣ ሄኖክ (የእታገኝ ልጅ) እና በላይ በቀለ ወያ ግጥሞቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ገጣሚ ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሹ) የአንድ ሰው ተውኔት የሚያቀርብ ሲሆን ድምፃዊያኑ ሙሉአለም ታከለና አበባው ጌታቸው በመሶብ ባላዊ ባንድ ታጅበው እንደሚያቀነቅኑ ተጠቁሟል፡፡ መድረኩ ከጉዞ አድዋ መስራቾች አንዱ በሆነው መሀመድ ካሳ የሚመራ ሲሆን  የመግቢያ ዋጋው 50 ብር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡  

Read 793 times