ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ወመዘክር የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከቀኑ 8፡00
ጀምሮ “አርበኝነትና ኢትዮጵያዊነት ከትላንት እስከዛሬ” በተሰኘ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ
ውይይት ያካሂዳል፡፡ በውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ የፒኤችዲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪና በቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ አማረ ፈንታው ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ የገለፀው ሚዩዚክ ሜይዴይ ፍላጎት ያለው በውይይቱ እንዲሳተፍ ጋብዟል፡፡
Saturday, 04 May 2019 15:10
“አርበኝነትና ኢትዮያዊነት ከትላንት እስከዛሬ” ላይ ዛሬ ውይይት ይካሄዳል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና