ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት “ያልታመመ አዕምሮን እንዴት ማከም ይቻላል” የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ምሽት ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በምሽቱም ኢ/ር ወንድሙ ነጋሽ (ከእንግሊዝ)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ኃ/ሚካኤል፣ ዶ/ር አበባየሁ ንጉሴ፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ፣ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ፣ የፍልስፍና መምህሩ ዮናስ ዘውዴ፣ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ፣ መምህርት እፀገነት ከበደ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ ኤፍሬም ስዩም፣ በቃሉ ሙሉ፣ ኤልያስ ሽታሁንና ህሊና ደሳለኝ በባህል ባንድ ታጅበው ግጥሞቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡