Print this page
Saturday, 18 May 2019 00:00

የሳይንቲስቱ የሕይወት ታሪክ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“የምድራችን ጀግና” በሚል ርዕስ በሳይንቲስቱ ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሄር የሕይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው መፅሐፍ ለገበያ ቀረበ
ዶ/ር ተወልደ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዛብህ ህይወት፣ በዘረመል ምህንድስና፣ በማሕበረሰብ መብት ባደረጉት ድርድርና ባስገኙት ውጤት እ.ኤ.አ በ2006 ዓ.ም ሲንጋፖር ላይ የተባበሩት መንግስታት ‹Champions of the Earth› (“የምድራችን ጀግና”) በማለት ሸልሟቸዋል፡፡
መጽሐፉ የሳይንቲስቱን ግለ ታሪክ ከልጅነት እስከ እውቀት ያካተተ ሲሆን ደራሲው ዘነበ ወላ፤ ይህንን ጥራዝ ለማዘጋጀት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ እንደፈጀበት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ መጽሐፉ በ59 ምዕራፎችና በ520 ገፆች ተቀንብቦ። በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲ ዘነበ ወላ ከዚህ ቀደም፣ “ሕይወት በባህር ውስጥ”፣ “ማስታወሻ”፣ “ልጅነት” እና “መልህቅ” በተሰኙ ስራዎቹ ይታወቃል፡፡

Read 6516 times