Saturday, 25 May 2019 07:59

የሳሚ ዳን “11ዱ ገፆች” አዲስ አልበም እየተደመጠ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በመጀመሪያው “ከራስ ጋር ንግግር” በተሰኘው አልበሙ ከፍተኛ ተቀባይነትን እና በርካታ ሽልማቶችን ያገኘው አርቲስት ሳሚዳን ሁለተኛ ሥራ የሆነው “11ዱ ገፆች” አዲስ አልበም እየተደመጠ ነው፡፡
በቅርቡ ለአድማጭ በደራሰው በዚህ አልበም ውስጥ 11 ያህል በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በማንነት ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ዘፈኖች የተካተቱ ሲሆን በአብዛኛው ግጥምና ዜማው በራሱ በሳሚዳን የተሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡ “ሀገርኛ” በተሰኘው ዘፈኑ ውስጥ ኦሮምኛን ከአማርኛ ቀላቅሎ የሰራ ሲሆን፤ የኦሮምኛ ግጥሙን አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ኃይለማሪያም ጽፎለታል፡፡
የሁሉንም ዘፈኖች ቅንብር ኤንዲ ቤተ ዜማ የሰራ ሲሆን በማስተሪንግና በተለያየ የሙዚቃ መሳሪያ በማጀብ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታን ጨመሮ በርካታ ባለሙያዎች መሳተፋቸውንና በሙዚቃ መሀል የሚደመጡ ትረካዎች በአንጋፋው ጋዜጠኛ ተዋናይና ገጣሚ ተፈሪ አለሙ መሰራቱም ታውቋል፡፡

Read 7919 times