Sunday, 26 May 2019 00:00

በቀጣዩ ሳምንት ትልቅ የፋሽን ትርኢት በወላይታ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 መኖሪያዋን በጣሊያን ባደረገችውና በፋሽኑ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፈችው ሞዴልና ዲዛይነር ሰናይት ዋንፒስ ዊንፒስ ፋሽን ኢቨንት በመተባበር የሚያዘጋጁት የፋሽን ትርኢት ግንቦት 25 ቀን 2011 በወላይታ ከተማ በጉተራ አዳራሽ ለታዳሚ እንደሚቀርብ ሞዴል ዲዛይነር ሰናይት ማሪዮ አስታወቀች፡፡
የኢትዮጵያን ባህልና አለባበስ ለመላው አፍሪካና አለም በማስተዋወቅ እውቅናና ሽልማትን ከተለያዩ የሽልማት ድርጅቶች የተቀበለችው ሞዴሏ ዘንድሮም የኢትዮጵያንና የመላው አፍሪካን አለባበስ በማጣጣም ዲዛይን አድርጋ ባዘጋጀቻቸው አልባሳት በጣሊያዊያንና በኢትዮጵያዊያን ሞዴሎች ለእይታ እንደምታቀርብ ገልፃለች፡፡
ሞዴልና ዲዛይነር ሰናይት በግንቦት 25ቱ ዝግጅት ከፋሽን ትርኢቱ በተጨማሪ ከጣሊያን ከተሞች አንዷ የሆነችውን ብራሲያኖን ከወላይታ ሶዶ ከተማ ጋር የእህትማማች ከተማነት ስምምነት ለመፈራረም የብራሲኖ ከተማ ልዑካን በወላይታ እንደሚገኙ አስታወቃ ሁለቱ ከተሞች በቀጣይ አብረው እንዲሰሩ ታደርጋለችም ተብሏል፡፡

Read 6733 times