Saturday, 25 May 2019 08:02

“ውብ እናት” የእናቶች የፋሽን ትርኢት ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

 የኔታ ኢንተርቴይመንትና ሃብል ሚዲያና ማስታወቂያ በመተባበር ያዘጋጁት “ውብ እናት” የእናቶች የፋሽን ትርኢት ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዲኤች ገዳ ታወር ይካሄዳል፡፡
ዘንድሮ የሚከበረውን የእናቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ የፋሽን ትርኢት ታዋቂና አንጋፋ አርቲስቶች የፋሽን ትርኢት ለታዳሚ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ በገጣሚያኑ ትዕግስት ማሞና ሰለሞን ሳህለ ግጥም፣ በሰዓሊያኑ ርብቃ ወንድምአገኝና ሄለን ተክሌ “እናትነት” የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ፣ ስታንዳፕ ኮሜዲ፣ በጳውሎስ ሆስፒታል ዶክተሮች የሚቀርብ ጥናታዊ ጽሑፍና በ “እንደ እኛ” የሙዚቃ ቡድን የሚቀርብ ሙዚቃ የፕሮግራሙ አካል ናቸው፡፡
በዕለቱም የክብር ዶ/ር አበበች ጐበና የኒያ ፋውንዴሽን (ኦቲዝም ማዕከል)  መስራች ዘሚ የኑስ፣ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ፣ ሎሬት የት ነበርሽ ንጉሴ፣ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ፣ የህፃናት መጽሐፍት ደራሲዋ ማርታ ዳዲ እና እናት ባንክ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ክብርና ምስጋና ይቀርብላቸዋል ተብሏል፡፡  

Read 7564 times