Saturday, 25 May 2019 09:19

ኢዜማ ሥራ አስፈፃሚዎቹን መረጠ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 ከሁለት ሳምንት በፊት የተመሰረተው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)፤ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ አባላትን አዋቀረ፡፡
የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ አባላቱን ያዋቀሩት የፓርቲው ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የፓርቲው መሪዎችና ዋና ፀሐፊው ተማርከው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ መሰረት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ናትናኤል ፈለቀ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ አቶ አመሃ ዳኛው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሰብሳቢ፣ ወ/ት ፅዮን እንግዳዬ የወጣቶች ጉዳይ ተጠሪ፣ ቴዎድሮስ አሰፋ በተመሳሳይ የወጣቶች ጉዳይ ተጠሪ፣ በመሆን የተመረጡ ሲሆን ወ/ሮ ናንሲ - ና ወ/ሮ ካውሰር ኢንዲሪስ አሊ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ሆነው ተሾመዋል፡፡ የሙያ ማህበራት ግንኙነት ተጠሪ ሆነው የተመረጡት ደግሞ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌና ወ/ሮ እሌኒ ነጋሽ ናቸው፡፡ አቶ ኢዮብ መሳፍንት የአለማቀፍ አባላት ተጠሪው ሆነዋል፡፡ እነዚህ ተሿሚዎች በሊቀ መንበሩ መዋቅር ስር ያሉ ናቸው ተብሏል፡፡
በፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስር ደግሞ የፓርቲው የመንግስት ጉዳይ ካቢኔ ሶስት እጩ ተወካዮች ተመርጠዋል - አቶ ኑሪ መደሲር፣ ዶ/ር ባንትይገኝ ታምራትና አቶ ተክሌ በቀለ፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉ የፓርላማ አባላት እጩ ተወካይ ሲሆኑ ኢ/ር ዳንኤል ሺበሺ የፌደሬሽን ም/ቤት እጩ ተወካይ ሆነው መመረጣቸው ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ። በዋናነት ዜግነትን የፖለቲካ መሰረቱ አድርጎ፣ በሃገሪቱ ማህበራዊ ፍትህ ማስፈን የሚል አላማን ያነገበ የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡
የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ሲሆኑ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው፡፡ ሊቀ መንበሩ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ ም/ሊቀመንበሩ ደግሞ ዶ/ር ጫኔ ከበደ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Read 8520 times