Saturday, 02 June 2012 10:19

የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በአዲስ መልክ ተመሰረተ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

በኢትዮጵያ በመንግስትና በግል የስፖርት መገናኛ ብዙሐን የሚሰሩ የስፖርት ጋዜጠኞች ባለፈው ረቡዕ በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ባደረጉት ጠቅላላ ጉባኤ የሙያ ማህበራቸውን በአዲስ መልክ በማደራጀት መሰረቱ፡፡በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በተደረገው የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር  መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአገሪቱ በሙያው የሚሰሩ ከ200 በላይ ባለሙያዎች ቢኖሩም በስፍራው የተገኙት ከ40 የማይበልጡ ነበሩ፡፡ በእለቱ በማህበሩ መተዳደርያ ደንብ ዙርያ አጭር ውይይት ቢደረግም በጠቅላላ ጉባዔው ዋና አጀንዳ መሰረት በቀጥታ የአዲሱን ስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ ማከናወን ተችሏል፡፡

በዚህ መሰረት በአዲስ መልክ በተመሰረተው የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በስራ አስፈፃሚነት የሚሰሩ ሰባት አባላት ተመርጠዋል፡፡ የአዲሱ የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው የኢቲቪ ስፖርት ክፍል ባልደረባ ዮናስ ተሾመ ሲሆን ምክትል ፕሬዝዳንት የኢንተር ስፖርት ማኔጂንግ ዲያሬክተርና የስፖርት 365 ሬድዮ ቶክሾው አቅራቢ ሁሴን አብዱልቀኒ፤ ዋና ፀሃፊ  የኢትዮ ስፖርት ማኔጂግ ዲያሬክተርና የኳስ ሜዳ ኮሜንታተር መንሱር አብዱልቀኒ እንዲሁም በገንዘብ ያዥነት የኤፍም አዲስ 96.3 ስፖርት አዘጋጅ አምሃ ፍሰሃ ሲሾሙ በኦዲተርነት የኢቢኤስ ባልደረባ የሆነው ዘርዓይ እያሱ እና የኢንተር ስፖርት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ብዙአየሁ ዋጋው ተመርጠዋል፡፡

 

 

 

 

 

Read 4820 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:30