Sunday, 26 May 2019 00:00

ሽዋዚንገር በአንድ የደቡብ አፍሪካ ጎረምሳ ድብደባ ተፈጸመበት

Written by 
Rate this item
(6 votes)


            በጀብደኛ ፊልሞቹ ሺህዎችን ሲረፈርፍና አፈር ከድሜ ሲያስግጥ የኖረው አሜሪካዊው የፊልም ተዋናይና የቀድሞ የካሊፎርኒያ ገዢ አርኖልድ ሽዋዚንገር ሰሞኑን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአንድ ጎረምሳ የድብደባ ጥቃት እንደደረሰበት ተዘግቧል፡፡
በደቡብ አፍሪካ በተዘጋጀው አርኖልድ አፍሪካ የተሰኘ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ታድሞ በነበረበት ወቅት በአንድ ግለሰብ ከጀርባው ሃይለኛ ቡጢ የቀመሰው ሽዋዚንገር፤ ምንም እንኳን የ71 አመት የእድሜ ባለጸጋ ቢሆንም በቡጢው አለመንገዳገዱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ “እንዲያውም መመታቴንም ያወቅሁት ከዙሪያዬ የነበሩት ሰዎች ግለሰቡን ለመያዝ ሲሞክሩና ግርግር ሲፈጠር ነው” ብሏል፤ሽዋዚንገር፡፡
ሽዋዚንገር ጆሃንስበርግ በሚገኘው ሳንድተን የስብሰባ ማዕከል ውስጥ በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ የሚቀርቡ ትርዒቶችን በሞባይሉ በመቅረጽ ላይ እያለ ከኋላው ደርሶ በቡጢ የደቃው ግለሰብ ወዲያውኑ በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የጠቆመው ዘገባው፤ በእነ ተርሚኔተርና ፕሪዲየተር ፊልሞች ላይ አገር ሲያንቀጠቅጥ የምናውቀው ፈርጣማው ሽዋዚንገር ግን በግለሰቡ ላይ ክስ እንደማይመሰረት አስታውቋል፡፡


Read 9119 times