Print this page
Tuesday, 04 June 2019 00:00

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት በሙዚቃ ዝርፊያ ሊከሰሱ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ሪቻርድ ካዌሳ የተባለው ታዋቂ ኡጋንዳዊ ድምጻዊ፤ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮሪ ሙሴቬኒ፣ ፈቃዴን ሳይጠይቁ ሙዚቃዬን ለምርጫ ቅስቀሳ በመጠቀም፣ የፈጠራ መብት ዘረፋ ፈጽመውብኛል በሚል ክስ ሊመሰርትባቸው መዘጋጀቱን ናይሮቢ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ በ2011 በተካሄደው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት “ዩ ዋንት አናዘር ታይም ዛት ራፕ” የተሰኘውን ተወዳጅ የሙዚቃ ስራውን ያለ ፈቃዱ እንደተጠቀሙበት የገለጸው ድምጻዊው፣ የፈጠራ መብቴን በመጣስ ላደረሱብኝ ጥቃት ባለፈው አመት 5 ቢሊዮን ሽልንግ እንዲከፍሉኝ በማመልከቻ ብጠይቃቸውም ፈቃደኛ አልነበሩም ብሏል፡፡
ለአገሪቱ የህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የአቤቱታ ደብዳቤውን ከሰሞኑ እንዳስገባ የገለጸው ድምጻዊው፣ ፕሬዚዳንቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠቀም ያለ ካሳ የማይከፍሉኝ ከሆነ ፍርድ ቤት እንደምገትራቸው ሊያውቁ ይገባል ሲል መናገሩን ዘገባው አመልክቷል::

Read 1269 times
Administrator

Latest from Administrator