Saturday, 08 June 2019 00:00

በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ ግንባታ ተጀመረ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  ከ6 ወር በኋላ “ሸገር ዳቦ”ን ለገበያ ያቀርባል

              በሰዓት 80ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተጣለ ሲሆን ፋብሪካው ከ6 ወር በኋላ ሲጠናቀቅ፣ “ሸገር ዳቦ” እያመረተ ለገበያ ያቀርባል ተብሏል፡፡ የፋብሪካውን ግንባታ  የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል የሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን የሚያከናውነው ሲሆን፤ በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ የዳቦ ማምረቻ ማሽኖች ግዢ ተከናውኖ እንደሚጠናቀቅና ከ6 ወራት በኋላም “ሸገር ዳቦ”  ለተጠቃሚዎች በአነስተኛ ዋጋ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
ፋብሪካው የሚገነባው በአዲስ አበባ አስተዳደር ሲሆን ለዳቦ ግብአት የሆነውን የስንዴ ዱቄትም እንደሚያመርትና ለገበያም እንሚያቀርብ ተነግሯል፡፡ 100 ግራም ዳቦ በ75 ሣንቲም ለገበያ ለማቅረብ ታቅዷል፡፡  የአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ፤ ከትላንት በስቲያ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለፋብሪካው ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡   

 

Read 1483 times