Saturday, 08 June 2019 00:00

3ኛው ዓመት “ሆሄ የስነ ፅሁፍ ሽልማት” ጳጉሜ 3 ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ኖርዝ ኢስት ኢንቨስት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው 3ኛው ዙር “ሆሄ የስነ ፅሁፍ ሽልማት” ጳጌሜ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄል፡፡
በሀገራችን የንባብ ባህል እንዲዳብርና የድርሰት ፈጠራ ስራዎች እንዲበረታቱ ለማድረግ በማሰብ በየዓመቱ በሚዘጋጀው በዚህ ስነ ፅሁፍ ሽልማት ላይ በአማርኛ፣ በትግርኛና በኦሮሚኛ የተሰናዱ የህፃናት መፅሃፍት፣ የረጅም ልቦለድ፣ የግጥም፣ የትምህርት ወይም የምርምርና የማህበራዊ ሚዲያ ፀሐፊዎች ወግ ለውድድር ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
በዘንድሮ ሽልማት ላይ ለውድድር የሚቀርቡት ከመስከረም 1 ቀን እስከ ጳጉሜ 5 2010 ዓ.ም በአማርኛ የተፃፉ የግጥም የረጅም ልቦለድ፣ የልጆች መፅሐፍት ሲሆኑ፣ በትግርኛና በኦሮምኛ የተፃፉ የ2009 ዓ.ም የልጆች መፃህፍት ለውድድር መቅረብ እንደሚችሉና ተወዳዳሪ መፅሀፍት ከሰኔ 1 ቀን እስከ 15 2011 ዓ.ም ማቅረብ እንደሚቻል የሽልማት ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ አሸናፊ መፅሀፍት፣ ለንባብ ከፍተኛ ውለታ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የመሰረታዊ ትምህርት ቀን በሚል በሚከበርበት ጳጉሜ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ሽልማትና እውቅና ያገኛሉ ተብሏል፡፡

Read 971 times