Saturday, 08 June 2019 00:00

“ብሌን የኪነ ጥበብ ምሽት 6” ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በየወሩ የሚያካሂደው ብሌን የኪነ ጥበብ ምሽት 6ኛው ዙር ምሽት ሰኞ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ን ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄል፡፡
ዋና ትኩረቱን በሰላም፣ በአንድነት፣ በፍቅርና በሀገራዊ መግባባት ላይ አድርጎ እያዝናና ግንዛቤን ያስጨብጣል በተባለው በዚህ ምሽት ላይ የተለያዩ የኪነ ጥበብ መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ሰዓሊ አገኘሁ አደነ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ፣ ዮናስ ዘውዴ፣ ፍሬዘር አድማሱ፣ ሄኖክ አየለ፣ ኤልያስ ሽታሁን እንደሪያስ ተረፈ ትዕግስት ማሞ፣ ባዩልኝ አያሌውና ሌሎችም የግጥም፣ የቅኔና የመነባንብ ስራቸውን እንደሚያቀርቡና በዚሁ ምሽት ታላቁ ሰው ሰለሞን ደሬሳ እንደሚዘከር የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ገልፆ፣ መግቢያው በነፃ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

Read 815 times