Print this page
Saturday, 08 June 2019 00:00

“ኮብላይ ዘመን” የግጥም መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


                 በገጣሚና ጋዜጠኛ ተሾመ ብርሃኑ የተገጠመው በርካታ ግጥሞችን የያዘው “ኮብላይ ዘመን” የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ከ65 በላይ ግጥሞችን በያዘው በዚህ መፅሐፍ ውስጥ በርካታ ፖተሊካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና የፍቅር ጉዳዮችን መዳሰሱን ገጣሚና ጋዜጠኛ ተሾመ በርሃኑ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
በ96 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ70 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ጋዜጠኛ ተሾመ ብርሃኑ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዝን በኤፍኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ላይ “ትዝታን በዜማ” በሚል ርዕስ በሚያቀርበው አዝናኝ ፕሮግራሙ ይበልጥ ይታወቃል፡፡


Read 926 times