Print this page
Saturday, 08 June 2019 00:00

የሰኔ ወር ዳጉ ሚዲያ “ምርጫና ሚዲያ” በኢትዮጵያ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በዳሪክ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን በየወሩ በተለያዩ ሚዲያ ነክ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚካሄደው ውይይት የሰኔ ወር መርሃ ግብር “ምርጫና ሚዲያ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በዳይመንድ ሆቴል ይካሄል፡፡
በዕለቱ ምርጫና ሚዲያ በኢትዮጵያ ምን መልክ እንደነበረውና ወደፊት ምን ሊመስል እንደሚገባው በባለሙያዎች ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በዕለቱ የመዝናኛ የድንገቴ እንግዳ፣ ሙያዊ ወግ እና ልዩ ልዩ መስተንግዶዎች እንደሚኖሩ የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ ገልጿል፡፡
ዳጉ የሚዲያ ውይይትና ሽልማት ፕሮግራም በየወሩ ከሚያካሂደው የሚዲያ ውይይት በተጨማሪ በዓመቱ መጨረሻ ለሚዲያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችና ተቋማትን የሚሸልምበት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ይኖረዋል ተብሏል፡፡     

Read 5950 times