Saturday, 08 June 2019 00:00

“ሾተል፣ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እኔ እንደገባኝ” ረቡዕ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የፍሊንት ስቶን ሆምስ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ፀደቀ ይሁኔ የፃፉት “ሾተል፣ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እኔ እንደገባኝ” የተሰኘ መፅሐፍ፤ የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ሳባ የስብሰባ አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ መፅሐፉ ከማህበራዊ እና ትምህርታዊ ፋይዳው አንፃር የሚገመገምበትና የሚተዋወቅበት መድረክ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡
“ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንደገባኝ የአንድን ትውልድ ሀገራዊ ስጦታ ለሚቀጥለው ትውልድ አሻሽሎ ማስተላለፍ ነው” የሚል ፅኑ እምነት ያላቸው ኢ/ር ፀደቀ ያዘጋጁት ይሄው መጽሀፍ፤ በከተማ ልማት አከታተምና ትራንስፎርሜሽን፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፣ የግልና የህዝብ ካፒታል ግንባታ ስርዓት አስተዳደር፣ ሀገረ-ወጥ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መረብ ኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ ገበያና የመንግስት ገቢ ትስስርና አስተዳደር፣ የትራንስፎርሜሽን ፋይናንስ፣ ግሽበትና ምንዛሪ፣ የግብርና ትራንስፎሜሽን ጤና ትምህርት፣ ውሃ ኢነርጂ፣ አይሲቲና ሌሎች በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል፡፡ በ518 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ150 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ ፀሀፍትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 5322 times