Print this page
Sunday, 16 June 2019 00:00

ምክር ቤቱ የምርጫ ቦርድ አባላቱን ሹመት ፀደቀ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡትን አራት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚሁ መሰረትም አቶ ውብሸት አየለ፣ ወ/ሪት ብዙወርቅ ከተተ፣ ዶ/ር ጌታሁን ካሣ እና ዶ/ር አበራ ደገፉ የቦርዱ አባል ሆነው ተሹመዋል፡፡ ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡
ቀደም ሲል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት የሚመሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፤  አሁንም በሰብሳቢነታቸው እንደሚቀጥሉ የተገለፀ ሲሆን፤ አቶ ውብሸት አየለ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ፣ ቦርድ ከምርጫው እየተቃረበ መሄድ ጋር ተያይዞ ሥራውን በአግባቡ ለመስራት እንዳይችል እንቅፋት ሆኖ የቆየው የአባላቱ አለመሟላት ችግር፣ አሁን መፍትሔ በማግኘቱ በቀጣይ ቦርዱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና ከምርጫ ዝግጅት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን ዕድል የሚያገኝ መሆኑን የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

Read 953 times