Sunday, 16 June 2019 00:00

በአቶ አንዷለም የሚመራው የኢዜማ ቡድን ከመቀሌ ህዝብና ከአስተዳዳሪዎች ጋር ይወያያል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 በጋምቤላ እና በሶማሌ ክልል ህዝባዊ ስብሰባዎች ያደርጋል

                 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከትግራይ፣ ከጋምቤላ እና ከሱማሌ ክልል አስተዳዳሪዎች ጋር በአካባቢ ፀጥታ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ምክክር ያደርጋል ተብሏል፡፡
በፓርቲው ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ የሚመራው ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ መቀሌ በማቅናት ከክልሉ አስተዳደሮች ጋር በፀጥታ እና በወቅታዊ የሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ የሚመክር ሲሆን ህዝባዊ ስብሰባም በመቀሌ ያደርጋል ተብሏል፡፡
በፓርቲው የፌዴሬሽን ም/ቤት እጩ ኢ/ር ዳንኤል ሺበሺ የሚመራው ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ በማቅናት ተመሳሳይ ተግባር የሚፈፅም ሲሆን በፓርቲው ም/ሊቀ መንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ የሚመራው ቡድንም ወደ ጋምቤላ በማቅናት ተመሳሳይ ምክክር እና ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ወደ ሶስቱም ክልሎች የሚያቀኑት ቡድኖች በክልሎቹ ከሚያደርጉት ህዝባዊ ስብሰባ ጎን ለጎን በክልሎቹ የሚገኙ የፓርቲውን ፅ/ቤቶች በቁሳቁስ የማጠናከር ተግባር ያከናውናሉ ሲሉ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አባል አቶ ያሬድ አማረ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡

Read 5514 times