Sunday, 16 June 2019 00:00

“ታኪዮን” ረጅም ልቦለድ መፅሐፍ ሐሙስ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


            በደራሲ ዳንኤል ለገሰ (ዶ/ር) የተፃፈውና በፍቅር፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚጠነጥነው “ታኪዮን” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መፅሀፍ፤ የፊታችን ሐሙስ  ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ ቤት) እንደሚመረቅ የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት አስታወቀ፡፡
በ23 ርዕሶች የተከፋፈለው  ወጥ ልቦለድ መፅሐፉ፤ በ324 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ150 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በርካታ ደራሲያን፣ ስመጥር የኪነ ጥበብ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙና በርካታ ኪነ ጥበባዊ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑ አዘጋጁ ገልጿል፡፡

Read 4560 times